አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል በኢትዮጵያ እውቅ የሙዚቃና የኢቬንት ፕሮዳክሽን ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ሙዚቃዊ የሚታወቅበት ዝግጅት ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የሆነው ፌስቲቫል አንጋፋና አዳዲስ ሙዚቀኞችን እንዲሁም የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ አርቲስቶች የሰሯቸውን አዳዲስ ስራዎች ያቀርባል፡፡ የፌስቲቫሉ የምረቃ ስነ ስርዓት በ2012 ዓ.ም የተደረገ ሲሆን አላማውም የጃዝ ሙዚቃን ለአዲስ አበባ ማስተዋወቅ፣አለም አቀፍ የጃዝ ሙዚቀኞች ጋር የትስስር እድልና መድረክ መፍጠር ነው፡፡በጃዝ አለም ውስጥ ከሚታወቁ በፌስቲቫሉ ላይ ከተሳተፉ እውቅ ሙዚቀኞች መካከል ሀይሉ መርጊያ፣አለማየሁ እሸቴ፣ሳሙዔል ይርጋ፣ክብሮም ብርሃኔ እና ቃየን ላብ ይገኙበታል፡፡ የዚህ አመት ፌስቲቫል ከግንቦት 16-18 ቀን 2016 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓልን አጽንኦት ይሰጣል፡፡

ከግንቦት 16-18 ቀን 2016 ዓ.ም . አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከግንቦት 16-18 ቀን 2016 ዓ.ም . አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ተሳታፊዎች

ጆርጋ መስፍን

የኢትዮ ጃዝ ባንድ በሆነው የውዳሴ ባንድ መስራች ጆርጋ መስፍን ኢትዮጵያዊ ሳክስፎኒስት ሲሆን እንደ ጤዛ፣ውዳሴና ናይል ፕሮጀክት በተሰኙ ስራዎቹ በዓለም ሙዚቃ ላይ ተጽእኖ ፈጥሯል፡፡ ጆርጋ ሙዚቃን እራሱን በራሱ ያስተማረና በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የሚገኙ የጥንትና ብዝኃነት ያላቸው ድምጾች ተጽእኖ ያረፈበት ሙዚቀኛ ነው፡፡
ጆርጋ የኃይሌ ገሪማ ድንቅ ፊልም ለሆነው ጤዛ የማጀቢያ ሙዚቃን ያቀናበረ ሲሆን በዚህም ስራው በሃያ ሁለተኛው ካርቴጅ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ቤስት ሚዩዚክ ሴሌክሽን እንዲሁም ምርጥ አቀናባሪ በሚል ዘርፍ በዱባይ አምስተኛ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ተሸልሟል፡፡
ጆርጋ በአዲስ ጃዝ ፌስቲቫል የመጀመሪያው ቀን ግንቦት 16 ላይ ‘’ከሁሉ የላቀው ደግ‘’ የተሰኘውን አልበም የሚለቅ ሲሆን በዕለቱም የሙዚቃ ስራውን ያቀርባል፡፡

Jorga-Mesfin-Landscape-(photo-by-Sosina-Mengistu)

ማቲው ቴምቦ

ማቲው ቴምቦ በደቡብ የአፍሪካ ክፍል ከምትገኘው ዛምቢያ የተገኘ አፍሮ ፖፕ ሙዚቀኛ ሲሆን በሀገሩ እንዲሁም በውጭ ሀገራት ጎልቶ የሚታይ የዛምቢያ ሙዚቃ አምባሳደር ነው፡፡ ማቲው በአውሮፓ በሙዚቃ ጉዞ ላይ እንዳለ ‘ኒላ’ እንዲሁም ‘ካማልያ ንዲሙ’ ተብለው የተሰየሙና ‘ሴቭ ማይ ሶውል’ ከተሰኘው ሁለተኛ አልበሙ ላይ የሚገኙ እውቅ ነጠላ ዜማዎችን ፕሮዲውስ አድርጓል። ይህ አልበም ሬጌ አልበም ሲሆን በኔዘርላንድስ በ1993 የተቀዳ ነው፡፡ ማቲው “አንተም” የተሰኘው አልበሙ ላይ ለሚገኘው ‘ናንዴንጋ’ ለተሰኘው ሙዚቃው ምርጥ አፍሮ ፊውዥን ተብሎ በቦርን ኤንድ ብሬድ አዋርድስ በተሰኘ ሽልማት በ2008 ዓ.ም በዛምቢያ የተሸለመ ሲሆን አልበሙ የዛምቢያን አገር በቀል የሙዚቃ መሳሪያዎች የያዘ የመጀመሪያ ስራው ነበር፡፡ ማቲው በአሜሪካን ፔንስልቬኒያ ከሚገኘው ፒትስበርግ ዩኒቨርስቲ በኢትኖሚዩዚኮሎጂ በያዝነው የአውሮፓውያን አመት በፒኤችዲ የሚመረቅ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ‘ምቴንዴሬ’ (ሰላም) የተሰኘው አልበሙን በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡

ያሆ ባህላዊ ባንድ

ያሆ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን በቀድሞ ስሙ ኢትዮ ከለር በመባል ይታወቅ የነበረ ሲሆን ሲቋቋም ስድስት አባላት ነበሩት፡፡ ቡድኑ አሁን አስር አባላትን ማለትም አምስት ሙዚቀኞች፣ ሁለት ተወዛዋዦች ፣ሁለት ድምጻውያንን ያቀፈ ሲሆን ፤ስራዎቻቸውን በአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ፣ትግርኛ፣ጉራግኛ፣ሱማልኛ፣አደርኛ ወ.ዘ.ተ ያቀርባሉ፡፡
ያሆ ባንድ በቀድሞ አጠራሩ “ኢትዮ ከለር” በነበረ ወቅት ከሙዚቃዊ ጋር በመሆን አስር ሙዚቃዎችን የያዘ በስማቸው የተሰየመ አልበም ወደ ህዝብ አድርሷል። ቡድኑ በስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ስፔይን ወ.ዘተ የሙዚቃ ጉዞዎችን ያደረገ ሲሆን እንደ ግዛቸው ተሾመ፣ ቶካቶ መና (የወላይትኛ ሙዚቃ ተጫዋች)፣ ሃዋ (የሱማሊኛ ሙዚቃ ተጫዋች) ካሉ የባህል ሙዚቃ ተጫዋቾች ጋር አብሮ ሰርቷል፡፡ የባንዱ አባላት ወደ ዘጠኝ አመታት ያህል በጋራ የሰሩ ሲሆን አሁን በቋሚነት በየሳምንቱ አርብ አፍሪካን ጃዝ ቪሌጅ ከዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ጋር ይጫወታሉ፡፡

Dawit-Yifru

ዳዊት ይፍሩ

ዳዊት ይፍሩ ከ30 አመታት በላይ በዘለቀው የሙዚቃ ጉዞው በኢትዮጵያ የጃዝ ታሪክ ውስጥ ስመጥር ከሆኑ አቀናባሪዎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ አንጋፋው ሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ በሙዚቃ ውስጥ የፈጠረው ተጽእኖ እጅግ በጣም ጠንካራ ከመሆኑ የተነሳ በርካቶች መላው የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃን ቅርጽ የሰጠው እንደሆነ ይገልፃሉ። እንደ ሙሉቀን መለሰ ፣ ነዋይ ደበበና ኬኔዲ መንገሻ ያሉ እውቅ ድምጻውያንን የሙዚቃ ሞያን ፈር እንዳስያዘ የሞያ አጋሮቹ የሚናገሩ ሲሆን በቅርቡ በሙዚቃ መሳሪያ ብቻ የተቀነባበረ አልበሙን በሸክላ እንዲሁም በዲጂታል መተግበሪያዎች ለህዝብ ጆሮ ማድረሱ አይዘነጋም:: በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ የሙዚቃ ማኀበር ሊቀመንበርና አባል ሲሆን አሁንም ለጥበብና ለሙዚቃ ባለው ትጉህነት የአዲሱ ትውልድ ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኞችን እያበረታታ ይገኛል፡፡

ግርማ በየነ

ግርማ በየነ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ወርቃማ ጊዜያት ተብለው በሚጠቀሱት ጊዜያት የተሰሩት ሙዚቃዎች አሁን ከሚደመጡት ሙዚቃዎች እንዲለይ ካደረጉ አሬንጀሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ገጣሚ፣የዜማ ደራሲ፣አሬንጀር፣ቮካሊስት፣የተሳካለት ፒያኖ ተጫዋች እንዲሁም የባንድ መሪ ነበር፡፡ በርካቶች አሬንጀር ሲባል ወደ አእምሯቸው የሚመጣው ስም የ ዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ ነው፡፡ ነገር ግን የኢትዮጲክ እትሞችን ፕሮዲውስ እንዳደረገው ፍራንሲስ ፋልሴቶ ከሆነ የሸክላ ሙዚቃዎች እጅግ ይወደዱ በነበረ ወቅት ግርማ በየነ 65 ያህል ሙዚቃዎችን አሬንጅ አድርጓል፡፡ ግርማ በድምጻዊነት የተወሰኑ ሙዚቃዎችን የሰራ ሲሆን የበለጠ የሚታወሰው ግን አሬንጀርና ፒያኒስት በመሆኑ ነው፡፡

girma-beyene-2

ሴልሞር ቱኩድዚ

ሴልሞር ቱኩድዚ እውቅ ዚምባቢያያዊት ድምጻዊ ስትሆን የሙዚቃ ጉዞዋ የጀመረው አባቷ የሆነው የቀድሞው የዙምባብዌ እውቅ ድምጻዊ “አይ አም ዘ ፊውቸር” ለሚለው ዜማ ሳውንድትራክ እንድትሰራ ወደ ስቱዲዮ የወሰዳት ጊዜ ነበር፡፡ በሀገሯ እንዲሁም በአሜሪክ በርካታ ውድድሮችን ያሸነፈች ሲሆን በናይጄሪያና እንግሊዝ ደግሞ ለበርካታ ውድድሮች ታጭታለች፡
ሴልሞር እስከአሁን ስምንት አልበሞችን የሰራች ሲሆን ‘ኤክስፕሬሽንስ’ የተሰኘው በ2005 ዓ.ም የወጣው አልበሟ መኃል የሚገኘው ‘ኑቫ ያንጉ’ የተሰኘው ዜማ እጅግ ተወዳጅነትን በማትረፍ ለ’ናማ’ እንዲሁም ለ’ዚማ’ ውድድር ታጨች፤ በራሱ ዜማም “የአፍሪካን ኢንተርቴይመንት አዋርድ አሜሪካ” እና “ዚምባብዌ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ WECA” ውድድርን አሸነፈች። ከዚያም በተጨማሪ በ2007 ዓ.ም ያወጣችው ‘አይ አም ዉማን’ የተሰኘወሰ አምስተኛ አልበሟ ‘ዝቪዲኪዲኪ’ በተሰኘው ሙዚቃ የ’ናማ’ ውድድርን አሸንፋለች፡፡

አፍሪጎ ባንድ

አፍሪጎ ባንድ በ1967 ዓ.ም የተመሰረተ የዩጋንዳ የሙዚቃ ቡድን ሲሆን የተመሰረተውም በአንጋፋው ሙዚቀኛና አቀናባሪ ሞስስ መቶቩ ፣ ቻርልስ ስካያንዚ፣ ጄፍ ሲዌቫ፣ ፓዲ ኤንሰቡጋ፣ ፓውሎ ሴርማጋ፣ ፍሪ ሉያምብያ፣ አንተኒ ካያን እንዲሁም ጄፍሪ ከዚቶ በተሰኙ ሌሎች ሰባት አባላት ነው፡፡ የባንዱ ሙዚቃ የዩጋንዳ ምቶች፣የኮንጎሊዝ ሱኩስ እንዲሁም ሌሎች የምስራቅ አፍሪካና የምዕራባውያን የሙዚቃ ይዘቶች የተቀየጡበት ነው፡፡ አፍሪጎ ባንድ የመድረክ ላይ አጨዋወታቸው እንዲሁም በሚስበው የሙዚቃ ምታቸው በፍጥነት ተወዳጅነትንና እውቅናን ማግኘት ችለዋል፡፡ ባንዱ ባለፉት አመታት በርካታ አልበሞችን ያደረሰ ሲሆን ይህም በ1970 ዓ.ም የወጣውን ዶክተር ከዊሳ የተሰኘውንና በፍጥነት ተወዳጅነትን ያተረፈውን የመጀመሪያ አልበማቸውን ያካትታል፡፡ ባንዱ ባለፉት አመታት በርካታ አባላቱን በመቀየር በዩጋንዳ እውቅ ከሆኑ ሙዚቀኞች መካከል የተወሰኑትን ማፍራት ችሏል ከእነዚህም ውስጥ ጆዋኒታ ካዋልያ፣ ሬቸል ማጉላ እና ሞስስ መቶቩ ይካተታሉ፡፡ አፍሪጎ ባንድ በመላው ዓለም የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከበርካታ ዓለም አቀፍ አርቲስቶች ጋርም በጋራ ሰርቷል፡፡ ባንዱ በምስራቅ አፍሪካ ካሉ ባንዶች እጅግ ስኬታማ ከሚባሉት መካከል ይጠቀሳል፡፡

መሐሪ ብራዘርስ

መሐሪ ብራዘርስ የተመሰረተው በ1998 ዓ.ም ሲሆን መስራቾቹም ሄኖክ መሐሪ (የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ምሩቅ፣ ፒያኒስትና መሪ ድምጻዊ) ፣ ሮቤል መሐሪ (የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ምሩቅና ጊታሪስት) ፣ ልዋም መሐሪ (ቤዝ ጊታሪስት) እና ሀላል መሐሪ (ድራመር) ናቸው፡፡ አሁን ቡድኑ ተስፋማሪያም ኤልያስ (ኪቦርድ) ፣ዘሪሁን በለጠ (ሳክስፎን) ፣ ለታሪክ ጥላሁን (ሳክስፎን) ፣ያሬድ ታደሰና (ከበሮ ፣) ሚሊዮን አድነውን (ኮንጋ) በተጨማሪነት ይዞ ይገኛል፡፡ባንዱ እንደ መሀሙድ አህመድ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ፣ ዳዊት መለሰ፣ዘሪቱ ከበደ፣ አለማየሁ እሸቴ፣ቴዲ አፍሮ፣ጆኒ ራጋ፣ ሚካኤል በላይነህ እንዲሁም ሌሎች አንጋፋ አርቲስቶች ጋር በጋራ ሰርቷል በተለያዩ ዓለማትም ዞረዋል፡፡
የባንዱ ፒያኒስትና መሪ ድምጻዊ ሄኖክ መሐሪ የባንዱ አባላት ከሆኑ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ሶስት አልበሞችን የሰሩ ሲሆን በ 2008 ዓ.ም የወጣውና 15 ሙዚቃዎችን በውስጡ የያዘው ‘790’ የተሰኘው አልበሙ በጊዜው ከወጡ አልበሞች እጅግ ስኬታማው ነበር።

ዮሃና ሳህሌ

ዮሃና ሳህሌ መቀመጫዋን አዲስ አበባ ያደረገች ድምጻዊት ስትሆን የሙዚቃ ትምህርቷን በመካነ እየሱስ የጃዝ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በ2010 ዓ.ም አጠናቃለች፡፡
ዮኃና ድምጿን በአግባቡ መጠቀምን ተክናበታለች ይህም ሙዚቃዋ ላይ ምን ያህል እንደሰራችና ለሙዚቃ ያላትን ፍቅር የሚያሳይ ነው፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ መሃሙድ አህመድ የተጫወተውን ‘ትዝታ’ የተሰኘውን ሙዚቃ በራሷ መንገድ በግሩም ሁኔታ በመጫወቷ የበለጠ እውቅናን አስገኝቶላታል። በአሁን ሰዓትም በደቡብ ፈረንሳይ ረዘም ላለ ጊዜያት በቆየችባቸው ጊዜያት የተፀነሰውን የመጀመሪያ አልበሟን ለማውጣት በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡

ሮሃ ባንድ

ሮሃ ባንድ የተመሰረተው በዳዊት ይፍሩ፣ ጆቫኒ ሪኮ፣ ሰላም ስዩም፣ፍቃደ አምደመስቀል፣ተክሌ ተስፋዝጊና ሌቨን ፎንዳቺ ነው፡፡ በ1970ዎቹና 80ዎቹ የሙዚቃውን ዓለም የተቆጣጠረ እጅግ በጣም ተወዳጅ ኢትዮጵያዊ ባንድ ሲሆን ዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃዎችን ይጫወት ነበር፡፡ ባንዱ እንደ አስቴር አወቀ፣ጥላሁን ገሰሰ፣መሀሙድ አህመድና አለማየሁ እሸቴ ካሉ ድምጻውያን ጋር ከ250 በላይ ሙዚቃዎችን ሰርቷል፡፡ ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ መፍጠር የቻለ ባንድ ሆኗል፡፡
ከ 1970ዎቹ እስከ 1980 ዎቹ የሮሃ ባንድ በመላው አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም አሜሪካ በተጨማሪም በአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች ተጉዟል፡፡ ዶ/ር ሙላቱ አስታጥቄ በ1979 ዓ.ም ሮሃ ባንድ በፓሪስና በስፔይን ትርዒታቸውን በሚያቀርቡ ወቅት አብሯቸው አቅርቧል፡፡ ሮሃ ባንድ የሙዚቃ ጉዞ አልበም የተቀረጸው በ1982 ዓ.ም በሮሃ ባንድ የመጀመሪያ የሰሜን አሜሪካን የሙዚቃ ጉዞ ወቅት ሲሆን ይህ አልበም ነዋይ ደበበ፣ሀመልማል አባተና ብርሃኔ ኃይሌን ለህዝብ አስተዋውቋል፡፡

ፕሮግራም

ዕለት 1

የግንቦት 16 መርሀ ግብር

ከምሽቱ 12:00
በሮች ይከፈታሉ
ከምሽቱ 01:00
ያሆ ባህላዊ ባንድ
ከምሽቱ 02:20
ማቲው ቴምቦ
ከምሽቱ 03:30
ጆርጋ መስፍን

ዕለት 2

የግንቦት 17 መርሀ ግብር
 
ከምሽቱ 12:00
በሮች ይከፈታሉ
ከምሽቱ 01:00
ሴልሞር ሙቱኩዚ
ከምሽቱ 02:10
አፍሪጎ ባንድ
ከምሽቱ 03:30
ዳዊት ይፍሩ እና ግርማ በየነ

ዕለት 3

የግንቦት 18 መርሀ ግብር

ከምሽቱ 12:00
በሮች ይከፈታሉ
ከምሽቱ 01:00
መሐሪ ብራዘርስ
ከምሽቱ 02:10
ዮሃና ሳህሌ
ከምሽቱ 03:20
ሮሃ ባንድ

ዕለት 1

ቅዳሜ, ሚያዚያ 21

8:00 ሰዓት
በር ይከፈታል
9:00 – 10:00 ሰዓት
ያንግ አዲስ እና ለታሪክ
10:30 – 11:30 ሰዓት
የሙዚቃዊ አርቲስቶች
12:00 -1:00 ሰዓት
ጆርጋ መስፍን
1:30 – 2:30 ሰዓት
ጎንደር ፋሲለደስ
3:00 ሰዓት

ክለብ ኪለርስ

ዕለት 2

እሁድ, ሚያዚያ 22 

8:00 ሰዓት
በር ይከፈታል
9:00 – 10:00 ሰዓት
የኢትዮጵያ ልጅ
10:30 – 11:30 ሰዓት
የሙዚቃዊ አርቲስቶች
12:00 – 1:00 ሰዓት
ዳዊት ይፍሩ
1:30 – 2:30 ሰዓት
ጎንደር ፋሲለደስ
3:00 ሰዓት
ክለብ ኪለርስ

For all general inquiries, please email info@addisjazzfestival.com

Scroll to Top