AddisJazzfestival_logo_cut

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል እንዲሁም የአፍሪካ ቀን ክብረ-በዓል ከግንቦት 16-18 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይካሄዳል

በሉሲ ኢላዶ

‘’ምንም እንኳን ጃዝ ረዥምና ብዙ የተነገረለት ታሪክ ቢኖረውም፤ይህ ማለት በለውጥ ሂደት ውስጥ ማለፉን አቁሟል ማለት አይደለም፡፡ የፈጠራ ባለሞያዎች ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለዓለም ልዩ ቅኝቶችንና አስደማሚ ክህሎቶችን በማሰተዋወቅ የዘርፉን ቅርጽ በተደጋጋሚ እየቀየሩት ይገኛሉ ፡፡’’

የአሜሪካ ጃዝ በርካታ መሰረቱ አፍሪካ ውስጥ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት የመጀመሪያዎቹ የዘርፉ ሙዚቀኞች አፍሪካ አሜሪካዊ በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን የዘር ሀረጋቸው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ባሻገር የሚመዘዘው ቅድመ–አያቶቻቸው ተጽእኖ ስላረፈባቸው ነው፡፡ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የዘር ልዩነት/መድልዎና የምዕራባውያን አስተሳሰቦች ጥቁር አሜሪካውያን ላይ በመጫን በነበሩባቸው ጊዜያት፣ጃዝ የራሳቸውን ድምጽ ማግኘት እንዲችሉ የረዳ ወሳኝ አካል ነበር፡፡ ጥቁር አሜሪካውያን በጊዜው የተጣለበቸውን ጫና ተቃውመው ሁሉንም መደበኛ ህጎች በመጣስ አሁን በዓለም ላይ ቁንጮ ተደርጎ የሚታሰብ የሙዚቃ ዘርፍ ፈጠሩ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሙዚቀኞች ከተለያዩ የባህላዊ ሙዚቃ አይነቶች ጋር ሙዚቃውን በማቀላቀላቸው የተነሳ በአፍሪካ የአሜሪካ ጃዝ በለውጥ ሂደት ውስት እያለፈ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ በኢትዮ ጃዝ አማካይነት (በሙላቱ አስታጥቄ የተፈጠረ የሙዚቃ ዘርፍ ነው) ይህንን ለውጥ ከተቀበሉት አገራት ውስጥ አንዷናት፡፡

ሙላቱ አስታጥቄ ፔንታቶኒክ መሰረት ያላቸውን የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃዎች ከ12 ኖት የምዕራባውያን ጃዝና የሙዚቃ መሳሪያዎች ጋር በማዋሃድ ኢትዮ ጃዝ የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ ዘርፍ ሊፈጥር ችሏል፡፡ ከሙላቱ ሌላ፣እንደ ኃይሉ መርጊያ እና አሁን በህይወት የሌለው ዓለማየሁ እሸቴ ሙዚቃው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅነት እንዲኖረው አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

‘’ለሙላቱ አስታጥቄ እውቅና ሳትሰጥ ስለኢትዮጵያ ሙዚቃ ማውራት አይቻልም’’ ይላል የሙዚቃዊ መስራች ተሾመ ወንድሙ፡፡ የኢትዮ–ጃዝ ፈር ቀዳጅ እንደመሆኑ ስራዎቹ በዓለም የተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ በርካታ በሱ እድሜ የሚገኙ እኩዮቹና አድማጮች ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘቱ ኢትዮጵያን በጃዝ ሙዚቃ ካርታ ላይ አስፍሯታል፡፡

ለዘርፉ ፍላጎት ያላቸው የጃዝ አድማጮችና አርቲስቶች ቁጥራቸው በአስገራሚ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን ይህም ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ‘’በጃዝ ስፍራው ያለው ክፍተት እድል እንዳለ አመላከተን’’ ይላል ተሾመ፡፡’ ‘’ጃዝ ፌስቲቫሎችን የሚያዘጋጁ ፕሮሞተሮች ነበሩ ነገር ግን እንቅፋቱ ቀጣይ አለመሆኑ ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ያንን ክፍተት ይሞላል ብለን የምናስበውን ፅንሰ–ሀሳብ ፈጠርን፡፡ ፅንሰ–ሀሳቡን የፈጠርንበት ተጨማሪ ምክንያት የበለጠ አገር–በቀልና ዓለም አቀፍ የጃዝ ሙዚቀኞች በአዲስ አበባ ስራቸውን እንዲያቀርቡ እንዲሁም የጃዝ ሙዚቃ እድገትና ልማት ላይ ተጽእኖ መፍጠር የሚችል የባህል ልውውጥ የማድረግ እድል እንዲያገኙ ለማየት ስለምንመኝ ነው፡፡’’

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል የሀገሪቱ የመጀመሪያ አገር በቀል የጃዝ ፌስቲቫል ሲሆን ዝግጅቱ በዚህ አመት ከግንቦት 16-18 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ አፍሪካን ፋዝ ቪሌጅ ይካሄዳል፡፡ ዝግጅቱ ሚያዝያ 2014 ዓ.ም በተቋቋመው አዲስ የሙዚቃ ኩባንያ በሆነው ሙዚቃዊ ነው የተዘጋጀው፡፡

ፌስቲቫሉ አንጋፋው አፍሪጎ ባንድ ከዩጋንዳ፣ ምርጧ ድምጻዊ ሴልሞር ቱኩድዚ ከዚምባብዌ፣ ማቲው ቴምቦ ከዛምቢያ፣ የኢትዮጵያን ዘመናዊ ሙዚቃ መልክ ከማስያዝ አንስቶ የሮሃ ባንድ ድምቀት እስከ መሆን የሚጠቀሰው አንጋፋው ዳዊት ይፍሩን እንዲሁም አንጋፋው ግርማ በየነን በተጨማሪም እንደ ጆርጋ መስፍን፣ ያሆ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ፣ መሐሪ ብራዘርስና ዮሃና ሳህሌ ተካተውበታል፡፡ የዚህ አመት ፌስቲቫል በልዩ ሁኔታ ለእውቁ ሙዚቀኛ ጆርጋ መስፍን የአልበም ምርቃት እንዲሁም ለአፍሪካ ቀን ትኩረት በመስጠት ይካሄዳል፡፡ ኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ ፕሮጀክት ሰላም ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመሆን ከሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን ከዓላማዎቹም መካከለ የአፍሪካ አገራት 2022 . ከብሔራዊ በጀታቸው 1% ያህሉን ለኪነጥበብ፣ባህልና ቅርስ ዘርፎች  እንዲመድቡ ከፍተኛ የማግባባት ስራ ማከናወን ይገኙበታል፡፡

‘’ይህ የፈጠርነው መድረክ ዓለም አቀፍ የጃዝ ሙዚቃ ተሞክሮን ለአድማጮች ያቀርባል በተጨማሪም አገር በቀል የጃዝ ሙዚቀኞች ለበርካታ ህዝብ ተሰጧቸውን እንዲያቀርቡና መድረኩን ከዓለም አቀፍ ሙዚቀኞች ጋር በመጋራት የትስስርና የትብብር እድሎችን እንዲያገኙ ያደርጋል’’  ይላል ተሾመ፡፡  ‘’በርከት ያሉ ተሰጥኦ ያላቸው የጃዝ ሙዚቀኞች አሉን ነገር ግን በርካቶቹ በባሮች፣ሬስቶራንቶችና የድርጅት ዝግጅቶች ላይ አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ሰዎች ነው ስራቸውን ለማቅረብ እድሉን የሚያገኙት፡፡’’

ተሾመ ይህን መሰል ተሞክሮ  ሀገር በቀል ሙዚቀኞችን እንደሚያሳድግ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለጃዝ ሙዚቃ ያለውን ገበያ በማስፋፋት ተሰጥኦ ያላቸው በርካታ ሙዚቀኞች ወደ ጃዝ እንዲያዘነብሉ እንደሚገፋፋ ተስፋ ያደርጋል፡፡ የፌስቲቫሉ የረዥም ጊዜ እቅዶች በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ የጃዝ ሙዚቃ ፌስቲቫል መሆን፣የሙዚቃ ወዳጆችን ከመላው ዓለም መሳብና አዲስ አበባ ከተማን የአፍሪካ ጃዝ ሙዚቃ መናኃሪያ ማድረግ፣አገር በቀል ቱሪዝምንና የመስተንግዶ ዘርፉን በስራ ፈጠራ ማሳደግ ናቸው፡፡ ‘’በርካታ ቁጥር ያላቸው አገር በቀልና ዓለም አቀፍ የጃዝ ሙዚቀኞች ፌስቲቫሉ ላይ ዝግጅታቸውን ሲያቀርቡ ይህም በኢትዮጵያ የጃዝ ሙዚቃ እድገትና ልማት ላይ ተጽእኖ ሲያሳርፍ ለማየት እንፈልጋለን’’ ይላል፡፡

‘’አላማችን የጃዝ ሙዚቃ አድማጮችን ማስፋት ነው’’ ይላል ተሾመ፡፡ ‘’ልክ እንደ ሬጌ ወይም ሂፕ ሆፕ ጃዝ በትክክል ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ካላቸው ጥቂት የሙዚቃ ዘርፎች ውስጥ አንዱ ነው ነገር ግን ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው ይህ የሙዚቃ አይነት ብዙ ጊዜ ልብ አይባልም፡፡ ጃዝ የሚሰጠውን በርካታ ለፈጠራ የሚያመቹ ዕድሎችን ለተቀበሉና የራሳቸውን ዘይቤ ለፈጠሩ ሰዎች ክብር መስጠት በተለይም በወጣት ሙዚቀኞች ዘንድ ለጃዝ ቀጣይነት አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡’’

ፌስቲቫሉን ከማዘጋጀት በተጨማሪ ሙዚቃዊ ሙዚቃን ሪከርድ ማድረግ፣ፕሮዳክሽንና ፐብሊሺንግ እንዲሁም  አርቲስት ማኔጅመንት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡ እንደ ተሾመ ከሆነ ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች የሚያጋጥማቸው ከፍተኛ እንቅፋት ሙዚቃ ማሳተም ላይ ሲሆን ሙዚቃ ማሳተምም በአህጉሪቱ ለሚገኙ ደራሲዎችና ባለመብቶች ቁልፍ የገቢ ምንጭ ነው፡፡ በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ሙዚቃን ማሳተም ያልተነካ ሀብት ነው ይህም የሆነበት ምክንያት ስለኮፒ ራይት፣ሙዚቃ ማሳተም ስላለው እሴት እንዲሁም ስለሙዚቃ ኢንዱስትሪው  ቢዝነስ ያለው እውቀት ላይ ክፍተት በመኖሩ ነው፡፡

‘’የኢትዮጵያን ሙዚቃና ደራሲዎች ለዓለም በተቻለው መጠንና ትርጉም በሚሰጥ መልኩ ለማቅረብ እንዲሁም እነሱንም በአግባቡ ለመገልገል፣ ሙዚቃ ማሳተም  እኛ ለመስራት እጅግ ፍላጎት ካለን ዘርፍ ውስጥ የሚገኝ ነው’’ ሲል ተሾመ ይገልጻል፡፡ ‘’በአሁኑ ሰዓት የማሳተም መብቶችና የሮያልቲ ስብሰባን በተመለከተ ምንም አይነት ዘገባ የለም፡፡ በዘርፉ ስላለው ምርጥ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ እውቀት እንዳላን ባለድርሻ አካላት፣ የአርቲስቶች ሙዚቃ በሜታ ዳታ ደረጃ በአግባቡ እንደተመዘገበ የማረጋገጥ ኃላፊነቱን እኛ ወስደናል፡፡’’

ሌላ ሙዚቃዊ ለማቃለል የሚያስበው ተግዳሮት በሙዚቃና ቪድዮ ፕሮዳክሽን የቴክኒክ ችሎታዎች ላይ ያሉ ክፍተቶችን መሙላት ነው፡፡ ይህም በተለይ ለህዝብ የሚደርሱና ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚውሉ ስራዎች ከፍተኛ ጥራት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ ‘’ራዕያችን ለሙዚቃው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በሙሉ የሙዚቃ ልምምድ ፕሮግራም ማቋቋም ሲሆን ይህም ፕሮፌሽናል ስልጠና መስጠትና ክህሎትና ቢዝነሳቸውን ሲያዳብሩ አቅጣጫ መስጠትን ያካትታል’’ ይላል ተሾመ

ተሾመ በአህጉሪቷ ላይ ለሚገኙ ፌስቲቫሎች በሙሉ የገንዘብ ጉዳይ ተግዳሮት እንደሆነና ዓለም አቀፍ አርቲስቶችን በበለጠ ሁኔታ ተሳታፊ ለማድረግ ዘላቂ የገንዘብ ትስስር (funding network) መቁዋቁዋም አለበት ይላል ተሾመ፡፡ ፌስቲቫል ላይ ገንዘብ ለማዋል ፍቃደኛ የሆኑ አሁን ያሉ የመንግስትና የግል ዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነትን ማጠናከርም ያስፈልጋል፡፡ ‘’ስፖስንሰሮችን ማግኘት ዋነኛ ተግዳሮት ነው’’ ይላል ተሾመ፡፡ ‘’አብዛኛውን ጊዜ አንድ ዘርፍ ላይ ትኩረት ላደረገ ጉዳይ ስፖንሰር ማግኘት ከባድ ነው ነገር ግን እነዚህ አንድ ዘርፍ ላይ ትኩረት ያደረጉ በንጽጽር ከሌላው ዘርፍ ጋር ሲተያዩ አነስተኛ እውቅና ያላቸው ዘርፎች ከአንድ ፌስቲቫል ጎልተው የሚወጡ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የገንዘብ ድጋፍ ለኛ ወሳኝ ነገር ነው ስለዚህ አሁን ባለው ሰዓት አገር በቀል አርቲስቶችንና ጥቂት ዓለም አቀፍ አርቲስቶችን ነው ልናካትት የምንችለው፡፡ ነገር ግን በተለይም በአህጉሪቱ የሚገኙ የበለጡ አርቲስቶችን እንድናካትት ወደ ፊት የሚዘጋጁ ፌስቲቫሎች ድጋፍ እንደሚያገኙ ተስፋ አለን፡፡’’

አዲስ ጃዝ ፌስቲቫል ከኮኔክት ፎር ካልቸር አፍሪካ፣ አፍሪካ ኅብረት፣ የስዊድን ኤምባሲ፣ሙዚቃዊ፣ሰላም ኢትዮጵያ፣ብሪቲሽ ካውንስል እንዲሁም አፍሪካ ጃዝ መንደር ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው፡፡

Scroll to Top